26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

55|24|እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ

ናቸው፡፡

55|25|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|26|በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

55|27|የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡

55|28|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|29|በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ

ነው፡፡

55|30|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›

55|31|እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ

እናስባለን፡፡

55|32|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|33|የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ

ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)

55|34|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|35|በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም)

አትርረዱምም፡፡

55|36|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|37|ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን

አበረታው)፡፡

55|38|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|39|በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡

55|40|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|41|ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡

55|42|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡

55|43|ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡

55|44|በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡

55|45|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|46|በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡

55|47|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|48|የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡

55|49|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|50|በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡

55|51|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|52|በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡

55|53|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|54|የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ

(ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡

55|55|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

55|56|በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው

ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡

281

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!