26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

23|60|እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው

የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡

23|61|እነዚያ በመልካም ሥራዎች ይጣደፋሉ፡፡ እነሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡

23|62|ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር

መጽሐፍ አልለ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡

23|63|በእውነቱ (ከሓዲዎች) ልቦቻቸው ከዚያ (መጽሐፍ) በዝንጋቴ ውስጥ ናቸው፡፡

ለእነሱም ከዚህ ሌላ እነሱ ለርሷ ሠሪዎችዋ የኾኑ (መጥፎ) ሥራዎች አሏቸው፡፡

23|64|ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ፡፡

23|65|ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱም፡፡

23|66|አንቀጾቹ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር፡፡ በተረከዞቻችሁም ላይ ወደ

ኋላችሁ ትመለሱ ነበራችሁ፡፡

23|67|በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ኾናችሁ

(ትመለሱ ነበራችሁ ይባላሉ)፡፡

23|68|(የቁርኣንን) ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ

ነገር መጣባቸውን

23|69|ወይስ መልክተኛቸውን አላወቁምን ስለዚህ እነርሱ ለእርሱ ከሓዲዎች ናቸውን

23|70|ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበት ይላሉን አይደለም፡፡ እውነትን ይዞ መጣላቸው፡፡

አብዛኞቻቸውም እውነትን ጠይዎች ናቸው፡፡

23|71|አላህም ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ

በእርግጥ በተበላሸ ነበር፡፡ ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም

ከክብራቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡

23|72|ወይስ ግብርን ትጠይቃቸዋለህን የጌታህም ችሮታ በላጭ ነው፡፡ እርሱም ከሰጪዎች

ሁሉ በላጭ ነው፡፡

23|73|አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ፡፡

23|74|እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው፡፡

23|75|ባዘንንላቸውና ከጉዳትም በእነርሱ ያለውን ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ

የሚዋልሉ ኾነው ይዘወትሩ ነበር፡፡

23|76|በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም፡፡ አይዋደቁምም፡፡

23|77|በእነሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን

ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡

23|78|እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን

እንጅ አታመሰግኑም፡፡

23|79|እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፡፡ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡

23|80|እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ

ነው፡፡ አታውቁምን

23|81|ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡

23|82|«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን» አሉ፡፡

23|83|«ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ

የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡

23|84|«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)»

በላቸው፡፡

176

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!