26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

ሱረቱ አል ሙልክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

67|1|ያ ንግሥና በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡

67|2|ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ

ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡

67|3|ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ

ምንም መዛነፍን አታይም፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ «ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?»

67|4|ከዚያም ብዙ ጊዜ ዓይንህን መላልስ፡፡ ዓይንህ ተዋርዶ እርሱም የደከመ ኾኖ ወዳንተ

ይመለሳል፡፡

67|5|ቅርቢቱን ሰማይም በእርግጥ በመብራቶች (በከዋክብት) አጌጥናት፡፡ ለሰይጣናትም

መቀጥቀጫዎች አደረግናት፡፡ ለእነርሱም (ለሰይጣኖች) የእሳትን ቅጣት አዘጋጀን፡፡

67|6|ለእነዚያም በጌታቸው ለካዱት የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!

67|7|በውስጧ በተጣሉ ጊዜ፤ እርሷ የምትፈላ ስትኾን ለእርሷ (እንደ አህያ) ማናፋትን

ይሰማሉ፡፡

67|8|ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፡፡ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር ዘበኞችዋ

«አስፈራሪ (ነቢይ) አልመጣችሁምን?» በማለት ይጠይቋቸዋል፡፡

67|9|«አይደለም በእርግጥ አስፈራሪ መጥቶናል፡፡ አስተባበልንም፡፡ አላህም ምንንም አላወረደ

እናንተ (አውርዷል ስትሉ) በትልቅ ስህተት ውስጥ እንጅ አይደላችሁም አልን» ይላሉ፡፡

67|10|«የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን

ነበር» ይላሉ፡፡

67|11|በኀጢኣታቸውም ያምናሉ ለእሳት ጓዶችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡

67|12|እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡

67|13|(ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ፡፡ ወይም በእርሱ ጩሁ፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ

ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

67|14|የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀት ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ)

አያውቅምን?

67|15|እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም

ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡

67|16|በሰማይ ውስጥ ያለን (ሰራዊት) በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ

የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)

67|17|ወይም በሰማይ ውስጥ ያለን በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ

ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡

67|18|እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ ጥላቻዬም እንዴት ነበር!

67|19|ወደ አእዋፍ ከበላያቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች የሚሰበሰቡም ሲኾኑ

አላዩምን? ከአልረሕማን በቀር (ባየር ላይ) የሚይዛቸው የለም፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ተመልካች

ነው፡፡

67|20|በእውነቱ ያ እርሱ ከአልረሕማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የኾነ ሰራዊት ማነው?

ከሓዲዎች በመታለል ውስጥ እንጅ በሌላ ላይ አይደሉም፡፡

298

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!