26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

14|27|አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር)

በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል፡፡ ከሓዲዎችንም አላህ ያሳስታቸዋል፡፡ አላህም የሚሻውን

ይሠራል፡፡

14|28|ወደእነዚያ የአላህን ጸጋ በክህደት ወደ ለወጡት ሕዝቦቻቸውንም በጥፋት አገር

ወዳሰፈሩት (ወደ ቁረይሾች) አላየህምን

14|29|(አገሪቱም) የሚገቧት ስትኾን ገሀነም ናት፡፡ ምን ትከፋም መርጊያ!

14|30|ለአላህም ከመንገዱ ያሳስቱ ዘንድ ባላንጣዎችን አደረጉለት፡፡ «(ጥቂትን) ተጠቀሙ

መመለሻችሁም ወደ እሳት ነው» በላቸው፡፡

14|31|ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ በእርሱ ውስጥ ሽያጭና ወዳጂነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ

በፊት ሶላትን በደንቡ ይሰግዳሉ፡፡ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በምስጢርም በግልጽም ይለግሳሉ፡፡

(ስገዱ ለግሱም) በላቸው፡፡

14|32|አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ከሰማይም ውሃን ያወረደ በእርሱም ከፍሬዎች

ሲሳይን ለእናንተ ያወጣ መርከቦችንም በፈቃዱ በባሕር ላይ ይንሻለሉ ዘንድ ለናንተ የገራ

ወንዞችንም ለናንተ የገራ ነው፡፡

14|33|ፀሐይንና ጨረቃንም ዘወትር ኼያጆች ሲኾኑ ለእናንተ የገራ ሌሊትንና ቀንንም

ለእናንተ የገራላችሁ ነው፡፡

14|34|ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው

በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው፡፡

14|35|ኢብራሂምም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ

አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡

14|36|«ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣዖታት) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና፡፡ የተከተለኝም

ሰው እርሱ ከኔ ነው፡፡ ትእዛዜንም የጣሰ ሰው አንተ መሓሪ አዛኝ ነህ፡፡

14|37|«ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት (በካዕባ)

አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው)፡፡

ከሰዎችም ልቦችን ወደእነሱ የሚናፍቁ አድርግ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፡፡

14|38|«ጌታችን ሆይ! አንተ የምንደብቀውንም የምንገልጸውንም ሁሉ በእርግጥ ታውቃለህ፡፡

በአላህም ላይ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር አይደበቅም፡፡

14|39|«ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ ምሰጋና

ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡

14|40|«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን

ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤

14|41|«ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን

ማር፡፡»

14|42|አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች

በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡

14|43|(ወደ ጠሪው መልአክ) ቸኳዮች ራሶቻቸውን አንጋጣጮች ኾነው (ዓይኖቻቸው

ይፈጣሉ)፡፡ ዓይኖቻቸው ወደነርሱ አይመለሱም፡፡ ልቦቻቸውም ባዶዎች ናቸው፡፡

14|44|ሰዎችንም ቅጣቱ የሚመጣባቸውን ቀን አስፈራራቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት «ጌታችን

ሆይ! ወደ ቅርበ ጊዜ ድረስ አቆየን፡፡ ጥሪህን እንቀበላለንና መልክተኞቹንም እንከተላለንና»

ይላሉ፡፡ «ከአሁን በፊት (በምድረ ዓለም) ለእናንተ ምንም መወገድ የላችሁም በማለት

የማላችሁ አልነበራችሁምን» (ይባላሉ)፡፡

129

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!