26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

4|50|በአላህ ላይ ውሸትን እንዴት እንደሚቀጣጥፉ ተመልከት፡፡ ግልጽ ወንጀልም በርሱ

(በመቅጠፍ) በቃ፡፡

4|51|ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ዕድልን ወደ ተሰጡት አላየኸምን በድግምትና በጣዖት ያምናሉ፡፡

ለእነዚያም ለካዱት፡- እናንተ በመንገድ (በሃይማኖት) ከእነዚያ ካመኑት ይበልጥ የቀናችሁ

ናችሁ ይላሉ፡፡

4|52|እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው፡፡ አላህም የረገመው ሰው ለእርሱ ፈጽሞ ረዳትን

አታገኝለትም፡፡

4|53|በእውነቱ ለእነሱ ከንግሥናው ፋንታ አላቸውን ያን ጊዜ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ

ያለችውን ነጥብ ያህል አይሰጡም ነበር፡፡

4|54|ይልቁንም ሰዎችን (ሙሐመድን) አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን

ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን ታላቅንም ንግሥና ሰጠናቸው፡፡

4|55|ከእነሱም (ከይሁዶች) በእርሱ ያመነ አለ፡፡ ከእነርሱም ከእርሱ ያፈገፈ አለ፡፡

አቃጣይነትም በገሀነም በቃ፡፡

4|56|እነዚያን በተአምራታችን የካዱትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን፡፡ ስቃይን እንዲቀምሱ

ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡

4|57|እነዚያንም ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን

ገነቶች ዘልዓለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናገባቸዋለን፡፡ ለእነሱ በውስጥዋ

ንጹሕ ሚስቶች አሉዋቸው፡፡ የምታስጠልልን ጥላም እናገባቸዋለን፡፡

4|58|አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል፡፡ በሰዎችም መካከል

በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ (ያዛችኋል)፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን

ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡

4|59|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን

ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ

ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ

መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡

4|60|ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል

ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን

ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል፡፡

4|61|ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው (ቁርኣን)ና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ

መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡

4|62|እጆቻቸውም ባስቀደሙት (ጥፋት) መከራ በደረሰችባቸውና ከዚያም «ደግን ሐሳብና

ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት

ይኾናሉ

4|63|እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡

እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል

ተናገራቸው፡፡

4|64|ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጅ አልላክንም፡፡ እነሱም ነፍሶቻቸውን

በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ ቢመጡና አላህንም ምሕረትን በለመኑ መልክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን

በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ኾኖ ባገኙት ነበር፡፡

45

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!