26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

50|34|«በሰላም ግቧት ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡

50|35|ለነርሱ በውስጧ ሲኾኑ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡

50|36|ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን እነርሱ በኀያልነት

ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ የኾኑትን (ማምለጫ ፍለጋ) በየአገሮቹም የመረመሩትን አጥፍተናል፡፡

ማምለጫ አለን?

50|37|በዚህ ውሰጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ (በልቡ) የተጣደ ኾኖ

(ወደሚነበብለት) ጆሮውን ለጣለ ሰው ግሳጼ አለበት፡፡

50|38|ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ

ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡

50|39|በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት

ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡

50|40|ከሌሊቱም አወድሰው ከስግደቶችም በኋላዎች (አወድሰው)፡፡

50|41|(የሚነገርህን) አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን (ከመቃብራቸው

ይወጣሉ)፡፡

50|42|ጩኸቲቱን በእውነት የሚሰሙበት ቀን ያ (ከመቃብር) የመውጫው ቀን ነው፡፡

50|43|እኛ እኛው ሕያው እናደርጋለን፡፡ እንገድላለንም፡፡ መመለሻም ወደእኛ ብቻ ነው፡፡

50|44|የሚፈጥኑ ኾነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫው ቀን

ነው)፡፡ ይህ በእኛ ላይ ገር የኾነ መሰብሰብ ነው፡፡

50|45|እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ

ዛቻየን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ፡፡

ሱረቱ አል ዛሪያት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

51|1|መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡

51|2|ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡

51|3|ገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡

51|4|ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡

51|5|የምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡

51|6|(እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡

51|7|የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡

51|8|እናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡

51|9|ከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡

51|10|በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡

51|11|እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡

51|12|የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡

51|13|(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡

272

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!