26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

ጣዖትንም የተገዛ ሰው (ሃይማኖት) ነው፡፡ እነዚያ በጣም በከፋ ስፍራ ናቸው፡፡»

ከቀጥተኛውም መንገድ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡

5|61|በመጡዋችሁም ጊዜ (ወደእናንተ) ከክህደት ጋር በእርግጥ የገቡ እነርሱም ከርሱ ጋር

በእርግጥ የወጡ ሲኾኑ «አምነናል» ይላሉ፡፡ አላህም ይደብቁት የነበሩትን ነገር በጣም ዐዋቂ

ነው፡፡

5|62|ከእነርሱም ብዙዎቹን በኃጢአትና በበደል እርምንም በመብላታቸው የሚጣደፉ ሲኾኑ

ታያለህ፡፡ ይሠሩት የነበሩት ነገር በጣም ከፋ!

5|63|ቀሳውስቱና ሊቃውንቱ ከኃጢአት ንግግራቸውና እርምን ከመብላታቸው አይከለክሏቸውም

ኖሮአልን ይሠሩት የነበሩት ነገር በጣም ከፋ!

5|64|አይሁዶችም «የአላህ እጅ የታሰረች ናት» አሉ፡፡ እጆቻቸው ይታሰሩ ባሉትም ነገር

ይረገሙ፡፡ አይደለም (የአላህ) እጆቹ የተዘረጉ ናቸው፡፡ እንደሚሻ ይለግሳል፡፡ ከጌታህም ወደ

አንተ የተወረደው (ቁርኣን) ከእነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምራቸዋል፡፡

በመካከላቸውም ጠብንና ጥላቻን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ጣልን፡፡ ለጦር እሳትን ባያያዙ

(ባጫሩ) ቁጥር አላህ ያጠፋታል፡፡ በምድርም ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ፡፡ አላህም

አበላሺዎችን አይወድም፡፡

5|65|የመጽሐፉም ባለቤቶች ባመኑና (ከክህደትም) በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነሱ ኃጢኣቶቻቸውን

በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር፡፡

5|66|እነርሱም ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደእነሱ የተወረደውን መጽሐፍ ባቋቋሙ

(በሠሩበት) ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፡፡ ከእነሱ ውስጥ ትክክለኞች

ሕዝቦች አልሉ፡፡ ከእነሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ!

5|67|አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልክቱን

አላደረስክም፡፡ አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል፡፡ አላህ ከሓዲዎችን ሕዝቦች አያቀናምና፡፡

5|68|«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደእናንተ

የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው፡

፡ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ

ይጨምርባቸዋል፡፡ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን፡፡

5|69|እነዚያ ያመኑና እነዚያም አይሁዳውያን የኾኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም (ከነርሱ)

በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነና መልካምን ሥራ የሠራ ሰው በነርሱ ላይ ፍርሃት

የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡

5|70|የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው፡፡ ወደእነሱም

መልክተኞችን ላክን፡፡ ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን

አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ፡፡

5|71|ፈተናም አለመኖርዋን ጠረጠሩ፡፡ ታወሩም፣ ደነቆሩም፣ ከዚያም አላህ ከነርሱ ላይ

ጸጸትን ተቀበለ፡፡ ከዚያም ከእነሱ ብዙዎቹ ታወሩ፣ ደነቆሩም፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ

ተመልካች ነው፡፡

5|72|እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡

አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ!

በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት

ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

5|73|እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ ከአምላክም አንድ አምላክ

እንጅ ሌላ የለም፡፡ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት

በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡

59

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!