26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2|95|እጆቻቸውም ባሳለፉት (በሠሩት) ምክንያት ምን ጊዜም ፈጽሞ አይመኙትም፤ አላህም

በዳዮችን ዐዋቂ ነው፡፡

2|96|ከሰዎችም ሁሉ ከእነዚያም (ጣዖትን) ከአጋሩት ይበልጥ በሕይወት ላይ የሚጓጉ ኾነው

በእርግጥ ታገኛቸዋለህ፡፡ አንዳቸው ሺሕ ዓመት ዕድሜ ቢሰጥ ይወዳል፡፡ እርሱም ዕድሜ

መሰጠቱ ከቅጣት የሚያርቀው አይደለም፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

2|97|ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ

(ቁርኣኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ

ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡

2|98|ለአላህና ለመላእክቱ ለመልክተኞቹም ለጂብሪልም ለሚካልም (ሚካኤል) ጠላት የኾነ

ሰው አላህ ለ(እነዚህ) ከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡

2|99|ወዳንተም ግልጽ የኾኑትን አንቀጾች በእርግጥ አውርደናል፡፡ በርሷም አመጸኞች እንጂ

ሌላው አይክድም፤

2|100|ቃል ኪዳንንም ቃል በገቡ ቁጥር ከእነርሱ ከፊሉ ይጥለዋልን? (ያፈርሰዋልን?)፤

ይልቁንም አብዛኞቻቸው አያምኑም፡፡

2|101|እነርሱ ጋርም ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የኾነ መልክተኛ ከአላህ ዘንድ

በመጣላቸው ጊዜ ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ከፊሉ እነርሱ እንደማያውቁ ኾነው የአላህን

መጽሐፍ ከጀርባዎቻቸው ኋላ ጣሉ፡፡

2|102|ሰይጣናትም በሱለይማን (ሰሎሞን) ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት)

ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን

የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ

የተወረደውን ነገር (ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ

አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር

ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና

የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል

የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በኾኑ

ኖሮ (ባልሠሩት ነበር)፡፡

2|103|እነርሱም (አይሁዶች) ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ (በተመነዱ ነበር)፡፡ የሚያውቁ

ቢኾኑ ከአላህ ዘንድ የኾነው ምንዳ (ነፍሶቻቸውን ከሚሸጡበት) በላጭ ነው፡፤

2|104|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (ለነቢዩ) ራዒና አትበሉ፡፡ ተመለከትን በሉም፡፡ ስሙም፤

ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡

2|105|እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎቹም የካዱት በናንተ ላይ ከጌታችሁ የኾነ

መልካም ነገር መወረዱን አይወዱም፡፡ አላህም በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡

አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

2|106|ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን

እናመጣለን፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መኾኑን አታውቅምን?

2|107|አላህ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለርሱ ብቻ መኾኑን አታውቅምን? ለእናንተም

ከአላህ ሌላ ዘመድና ረዳት ምንም የላችሁም፡፡

2|108|በእውነቱ ከአሁን በፊት ሙሳ እንደተጠየቀ ብጤ መልክተኛችሁን ልትጠይቁ

ትፈልጋላችሁን? በእምነትም ክህደትን የሚለውጥ ሰው ትክክለኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ፡፡

2|109|ከመጽሐፉ ባለቤቶች ብዙዎች እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በኾነው

ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ሊመልሱዋችሁ ተመኙ፡፡ አላህም ትዕዛዙን

እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ፤ እለፏቸውም፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ ነውና፡፡

13

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!