26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

17|110|«አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤ (ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ

(መልካም ነው)፡፡ ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና» በላቸው፡፡ በስግደትህም (ስታነብ)

አትጩህ፡፡ በእርሷም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ በዚህም መካከል መንገድን ፈልግ፡፡

17|111|«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣

ለእርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው በልም፡፡ ማክበርንም አክብረው፡፡»

ሱረቱ አል ከህፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

18|1|ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ

ላወረደው ይገባው፡፡

18|2|ቀጥተኛ ሲሆን ከእርሱ ዘንድ የኾነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፣ እነዚያንም በጎ

ሥራዎችን የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን ሊያበስርበት፤

(አወረደው)፡፡

18|3|በእርሱ ውስጥ ዘለዓለም የሚቆዩበት ሲኾኑ (ያላቸው መኾኑን)፡፡

18|4|እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስፈራራበት (አወረደው)፡፡

18|5|ለእነሱም ለአባቶቻቸውም በርሱ ምንም እውቀት የላቸውም፡፡ ከአፎቻቸው የምትወጣውን

ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡

18|6|በዚህም ንግግር (በቁርኣን) ባያምኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን

ይፈራልሃል፡፡

18|7|እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መኾኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለእርሷ

ጌጥ አደረግን፤

18|8|እኛም በእርሷ ላይ ያለውን (በመጨረሻ) በእርግጥ በቃይ የሌለበት ምልጥ ዐፈር

አድራጊዎች ነን፡፡

18|9|የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራቶቻችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን

18|10|ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና «ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፤ ለእኛም

ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

18|11|በዋሻውም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው፡፡

18|12|ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ

አስነሳናቸው፡፡

18|13|እኛ ወሬያቸውን በአንተ ላይ በእውነት እንተርካለን፡፡ እነሱ በጌታቸው ያመኑ ጎበዞች

ናቸው፡፡ መመራትንም ጨመርንላቸው፡፡

18|14|(በንጉሣቸው ፊት) በቆሙና «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ

አምላክን አንገዛም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላን ብናመልክ) ወሰን ያለፈን (ንግግር) በእርግጥ ተናገርን፡፡

» ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን አጠነከርን፡፡

18|15|«እነዚህ ሕዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ፤ (እውነተኞች ከኾኑ) በእነርሱ

ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም በአላህም ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ

ማነው» (አሉ)፡፡

147

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!