26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

5|90|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን

ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ (እርኩስን) ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡

5|91|ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል

አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ (ከእነዚህ) ተከልካዮች

ናችሁን (ተከልከሉ)፡፡

5|92|አላህንም ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ተጠንቀቁም፡፡ ብትሸሹም፤ በመልክተኛችን

ላይ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ መኾኑን ዕወቁ፡፡

5|93|በእነዚያ ባመኑትና በጎ ሥራዎችን በሠሩት ላይ (ክህደትን) በተጠነቀቁና ባመኑ

መልካም ሥራዎችንም በሠሩ ከዚያም (የሚያሰክርንና ቁማርን) በተጠነቀቁና ባመኑ ከዚያም

(ከተከለከለው ሁሉ) በተጠነቀቁና (ሥራን) ባሳመሩ ጊዜ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት

ነገር ኃጢአት የለባቸውም፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡

5|94|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (በሐጅ ጊዜ) እጆቻችሁና ጦሮቻችሁ በሚያገኙት ታዳኝ

አውሬ አላህ ይሞክራችኋል፡፡ በሩቅ ኾኖ የሚፈራውን ሰው አላህ ሊገልጽ (ይሞክራችኋል)፡፡

ከዚያም በኋላ ወሰንን ያለፈና ያደነ ሰው ለርሱ አሳማሚ ቅጣት አለው፡፡

5|95|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንት በሐጅ ሥራ ውስጥ ስትኾኑ አውሬን አትግደሉ፡፡

ከእናንተም እያወቀ የገደለው ሰው ቅጣቱ ከእናንተ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የሚፈርዱበት

የኾነ ወደ ካዕባ ደራሽ መሥዋዕት ሲኾን ከቤት እንስሳዎች የገደለውን ነገር ብጤ መስጠት

ወይም ምስኪኖችን ማብላት ወይም የዚህን ልክ መጾም ማካካሻ ነው፡፡ (ይኽም) የሥራውን

ከባድ ቅጣት እንዲቀምስ ነው፡፡ (ሳይከለከል በፊት) ካለፈው ነገር አላህ ይቅርታ አደረገ፡፡

(ወደ ጥፋቱም) የተመለሰም ሰው አላህ ከርሱ ይበቀላል፡፡ አላህም አሸናፊ የመበቀል ባለቤት

ነው፡፡

5|96|የባሕር ታዳኝና ምግቡ ለእናንተም ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለናንተ

ተፈቀደ፡፡ በሐጅም ላይ እስካላችሁ ድረስ የየብስ አውሬ በናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ ያንንም

ወደርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡

5|97|ከዕባን፣ የተከበረውን ቤት፣ ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹንም

መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፡፡ ይህ አላህ በሰማያት ያለውን ሁሉ በምድርም

ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መኾኑን አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን እንድታውቁ ነው፡፡

5|98|አላህ ቅጣተ ብርቱ መኾኑን አላህም መሓሪ አዛኝ መኾኑን እወቁ፡፡

5|99|በመልክተኛው ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለበትም፡፡ አላህም የምትገልጹትን ነገር

የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል፡፡

5|100|«የመጥፎው (ገንዘብ) ብዛት ቢያስደንቃችሁም እንኳ መጥፎውና ጥሩው

አይስተካከሉም፡፡ ባለልቦች ሆይ! አላህንም ፍሩ፤ እናንተ ልትድኑ ይከጀላልና፤» በላቸው፡፡

5|101|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ፡፡

ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለናንተ ትገለጻለች፤ ከእርሷ አላህ ይቅርታ

አደረገ፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ ነው፡፡

5|102|ከናንተም በፊት ሕዝቦች በእርግጥ ጠየቋት፡፡ ከዚያም በእርሷ (ምክንያት) ከሓዲዎች

ኾኑ፡፡

5|103|ከበሒራ ከሳኢባም ከወሲላም ከሓምም አላህ ምንንም (ሕግ) አላደረገም፡፡ ግን

እነዚያ የካዱት በአላህ ላይ ውሸትን ይቀጣጥፋሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም አያውቁም፡፡

5|104|ለእነርሱም አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልክተኛው ኑ በተባሉ ጊዜ «አባቶቻችንን

በርሱ ላይ ያገኘንበት ነገር ይበቃናል» ይላሉ፡፡ አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና የማይመሩ

ቢኾኑም (ይኸንን ማለት ይበቃቸዋልን)

61

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!