26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

23|34|«ብጤያችሁም የኾነን ሰው ብትታዘዙ እናንተ ያን ጊዜ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናቸሁ»

(አሉ)፡፡

23|35|«እናንተ በሞታችሁና ዐፈርና አጥንቶችም በኾናችሁ ጊዜ እናንተ (ከመቃብር)

ትወጣላችሁ በማለት ያስፈራራችኋልን

23|36|«ያ የምትስፈራሩበት ነገር ራቀ፤ በጣም ራቀ፡፡

23|37|«እርሷ (ሕይወት) ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ እንሞታለን፤

(ልጆቻችን ስለሚተኩ) ሕያውም እንኾናለን፡፡ እኛም ተቀስቃሾች አይደለንም፡፡

23|38|«እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እኛም ለእርሱ

አማኞች አይደለንም» (አሉ)፡፡

23|39|(መልክተኛውም) «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ እርዳኝ» አለ፡፡

23|40|(አላህም) «ከጥቂት ጊዜ በኋላ (በጥፋታቸው) በእርግጥ ተጸጻቾች ይኾናሉ»

አለው፡፡

23|41|ወዲያውም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፡፡ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም

አደረግናቸው፡፡ ለበደለኞች ሕዝቦችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡

23|42|ከዚያም ከእነሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦች አስገኘን፡፡

23|43|ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜያዋን አትቀድምም፤ አይቅቆዩምም፡፡

23|44|ከዚያም መልክተኞቻችንን የሚከታተሉ ኾነው ላክን፡፡ ማንኛይቱንም ሕዝብ

መልክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት፡፡ ከፊላቸውንም በከፊሉ (በጥፋት) አስከታተለን፡፡

ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ ለማያምኑም ሕዝቦች (ከእዝነታችን) መራቅ ተገባቸው፡፡

23|45|ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን፡፡

23|46|ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ (ላክናቸው)፡፡ ኮሩም፡፡ የተንበጣረሩ ሕዝቦችም ነበሩ፡፡

23|47|«ብጤያችንም ለኾኑ ሁለት ሰዎች ሕዝቦቻቸው ለእኛ ተገዢዎች ኾነው ሳሉ

እናምናለን» አሉ፡፡

23|48|አስተባበሉዋቸውም፡፡ ከጠፊዎቹም ኾኑ፡፡

23|49|ሙሳንም (ነገዶቹ) ይምመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡

23|50|የመርየምን ልጅና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡ የመደላደልና የምንጭ ባለቤት

ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡

23|51|እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ

የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡

23|52|ይህችም (በአንድ አምላክ የማመን ሕግጋት) አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ

ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡

23|53|(ከዚያ ተከታዮቻቸው) የሃይማኖት ነገራቸውንም በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው

ቆራረጡ፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው፡፡

23|54|እስከ ጊዜያቸውም ድረስ በጥምመታቸው ውስጥ ተዋቸው፡፡

23|55|ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን

23|56|በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው መኾንን (ያስባሉን) አይደለም፤ (ለማዘንጋት መኾኑን)

አያውቁም፡፡

23|57|እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የኾኑት፡፡

23|58|እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራቶች ከሚያምኑት፡፡

23|59|እነዚያም እነርሱ በጌታቸው (ጣዖትን) የማያጋሩት፡፡

175

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!