26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

28|4|ፈርዖን በምድር ላይ ተንበጣረረ፡፡ ነዋሪዎቿንም የተከፋፈሉ ጓዶች አደረጋቸው፡፡ ከእነርሱ

ጭፍሮችን ያዳክማል፡፡ ወንዶች ልጆቻቸውን በብዛት ያርዳል፡፡ ሴቶቻቸውንም ይተዋል፤ እርሱ

ከሚያበላሹት ሰዎች ነበርና፡፡

28|5|በእነዚያም በምድር ውስጥ በተጨቆኑ ላይ ልንለግስ፣ መሪዎችም ልናደርጋቸው

ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን፡፡

28|6|ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንንና ሃማንንም ሰራዊቶቻቸውንም ከእነሱ

ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው (እንሻለን)፡፡

28|7|ወደ ሙሳም እናት «አጥቢው፣ በርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው

አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና» ማለትን

አመለከትን፡፡

28|8|የፈርዖን ቤተሰቦችም (መጨረሻው) ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት፡፡

ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸውም ሀጢአተኞች ነበሩ፡፡

28|9|የፈርዖንም ሚስት «ለእኔ የዓይኔ መርጊያ ነው፡፡ ለአንተም፡፡ አትግደሉት፡፡ ሊጠቅመን

ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አለች፡፡ እነርሱም (ፍጻሜውን) የማያውቁ ሆነው

(አነሱት)፡፡

28|10|የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ፡፡ ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ

ልትገልጸው ቀርባ ነበር፡፡

28|11|ለእኅቱም ተከታተይው አለቻት፡፡ እርሱንም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና

አየችው፡፡

28|12|(ወደናቱ ከመመለሱ) በፊትም አጥቢዎችን (መጥባትን) በእርሱ ላይ እርም

አደረግን፡፡ (እኅቱ) «ለእናንተ የሚያሳድጉላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን

ቤተሰቦች ላመልክታችሁን» አለችም፡፡

28|13|ወደእናቱም ዓይንዋ እንድትረጋ፣ እንዳታዝንም፣ የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን

እንድታውቅ መለስነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

28|14|ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ እንዲሁም

መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡

28|15|ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ጊዜ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ፡፡ በእርሷም ውስጥ

የሚጋደሉን ሁለት ሰዎችን አገኘ፡፡ ይህ ከወገኑ ነው፤ ይህም ከጠላቱ ነው፡፡ ያም ከወገኑ

የሆነው ሰው በዚያ ከጠላቱ በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው፡፡ ሙሳም በጡጫ መታው፡፡

ገደለውም፡፡ ይህ ከሰይጣን ሥራ ነው፡፡ እርሱ ግልጽ አሳሳች ጠላት ነውና አለ፡፡

28|16|«ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ለእኔም ማር አለ፡፡» ለእርሱም ምሕረት

አደረገለት እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

28|17|«ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ)፤

ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም አለ፡፡

28|18|በከተማይቱም ውስጥ ፈሪ የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ፡፡ በድንገትም ያ ትላንት እርዳታን

የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል፡፡ ሙሳ ለርሱ «አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ

ነህ» አለው፡፡

28|19|(ሙሳ) ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነውን ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ

«ሙሳ ሆይ! በትላንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር

ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን አትፈልግም»

አለው፡፡

199

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!