26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

4|124|ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው

እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡

4|125|እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ

ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ

አድርጐ ያዘው፡፡

4|126|በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት

ከባቢ ነው፡፡

4|127|በሴቶችም ነገር ያስተቹሃል፡፡ አላህ በእነርሱ ይነግራችኋል፡፡ ያም በመጽሐፉ በእናንተ

ላይ የሚነበበው በእነዚያ ለእነርሱ (ከውርስ) የተጻፈላቸውን በማትሰጧቸውና ልታገቧቸው

በማትፈልጉት የቲሞች ሴቶች (ይህንን እንዳታደርጉ) ከሕፃናትም ለኾኑት ደካሞች መብታቸውን

እንድትሰጡ ለየቲሞችም በትክክል አንድትቆሙ (ይነግራችኋል) በላቸው፡፡ ከበጎም ሥራ

ማናቸውንም ብትሠሩ አላህ እርሱን ዐዋቂ ነው፡፡

4|128|ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን

ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም፡፡ መታረቅም መልካም ነው፡፡ ነፍሶችም ንፍገት

ተጣለባቸው፡፡ መልካምም ብትሠሩ ብትጠነቀቁም አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

4|129|በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ

ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡

ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

4|130|ቢለያዩም አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ጥበበኛ

ነው፡፡

4|131|በሰማያት ያለውና በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያንም ከበፊታችሁ

መጽሐፍን የተሰጡትን እናንተንም አላህን ፍሩ በማለት በእርግጥ አዘዝን፡፡ ብትክዱም በሰማያትና

በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ (አትጐዱትም)፡፡ አላህም ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡

4|132|በሰማያት ያለውና በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ መመከያም በአላህ በቃ፡፡

4|133|ሰዎች ሆይ!(አላህ) ቢሻ ያስወግዳችኋል፡፡ ሌሎችንም ያመጣል፡፡ አላህም በዚህ ላይ

ቻይ ነው፡፡

4|134|የቅርቢቱን ዓለም ምንዳ የሚፈልግ የኾነ ሰው አላህ ዘንድ የቅርቢቱና የመጨረሻይቱ

ምንዳ አልለ፡፡ አላህም ሰሚ ተመልካች ነው፡፡

4|135|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትክክል (ፍትሕ) ቀዋሚዎች በነፈሶቻችሁ ወይም

በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም

ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ (ከእናንተ) ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡

፡ ብታጠምሙም ወይም (መመስከርን) ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

4|136|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው በዚያም በመልክተኛው ላይ

ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ፡፡ በአላህና በመላእክቱም፣

በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን፣ የካደ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት

በእርግጥ ተሳሳተ፡፡

4|137|እነዚያ (በሙሳ) ያመኑና ከዚያም (ወይፈንን በመገዛት) የካዱ ከዚያም (በእርሱ)

ያመኑ ከዚያም (በዒሳ) የካዱ ከዚያም (በሙሐመድ) ክሕደትን የጨመሩ አላህ ለእነሱ

የሚምራቸውና ቅኑን መንገድ የሚመራቸው አይደለም፡፡

4|138|መናፍቃንን ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት ያላቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡

4|139|እነዚያ ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ እነሱ ዘንድ ልቅናን

ይፈልጋሉን ልቅናውም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው፡፡

50

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!