26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

37|158|በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች

በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡

37|159|አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

37|160|ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡

37|161|እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤

37|162|በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡

37|163|ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡

37|164|(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን

እንጅ፡፡

37|165|እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡

37|166|እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡

37|167|እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-

37|168|«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤

37|169|«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»

37|170|ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡

37|171|(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡

37|172|እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

37|173|ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

37|174|ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡

37|175|እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡

37|176|በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?

37|177|በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!

37|178|እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡

37|179|ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡

37|180|የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡

37|181|በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤

37|182|ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡

ሱረቱ ሷድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

38|1|ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ

እንደሚሉት አይደለም)፡፡

38|2|ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡

38|3|ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና

የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡

234

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!