26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

41|10|በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ በውስጧም

ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ

ወሰነ፡፡

41|11|ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም

ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡

41|12|በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ በሰማይቱም ሁሉ ነገሯን

አዘጋጀ፡፡ ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን፡፡ (ከሰይጣናት) መጠበቅንም ጠበቅናት፡፡ ይህ

የአሸናፊው የዐዋቂው (ጌታ) ውሳኔ ነው፡፡

41|13|(ከእምነት) እንቢ «ቢሉም እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የኾነን መቅሰፍት

አስጠነቅቃችኋለሁ» በላቸው፡፡

41|14|መልክተኞቹ አላህን እንጅ ሌላን አትግገዙ በማለት ከስተፊታቸውም ከስተኋለቸውም

በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር፡፡ ስለዚህ እኛ በዚያ በእርሱ

በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» አሉ፡፡

41|15|ዓድም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?»

አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን?

በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ፡፡

41|16|በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸውም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻን ብርቱ

ነፋስ መናጢዎች በኾኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው፡፡ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ስቃይ በጣም

አዋራጅ ነው፡፡ እነርሱም አይረዱም፡፡

41|17|ሰሙዶችማ መራናቸው ዕውርነትንም በቅንነት ላይ መረጡ፡፡ ይሠሩትም በነበሩት

ኃጢኣት አሳናሽ የኾነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው፡፡

41|18|እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳንናቸው፡፡

41|19|የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነርሱም

የሚከመከሙ ኾነው ይነዳሉ፡፡

41|20|በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር

በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡

41|21|ለቆዳዎቻቸውም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ፡፡ «ያ አንዳቹን ነገር

ሁሉ ያናገረው አላህ አናገረን፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ጊዜ ፈጠራችሁ፡፡ ወደእርሱም

ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል፡፡

41|22|ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁም በእናንተ ላይ ከመመስከራቸው የምትደበቁ

አልነበራችሁም፡፡ ግን አላህ ከምትሠሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ፡፡

41|23|ይህም ያ በጌታችሁ የጠረጠራችሁት ጥርጣሪያችሁ አጠፋችሁ፡፡ ከከሳሪዎቹም ኾናችሁ

(ይባላሉ)፡፡

41|24|ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት፡፡ ወደሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ

እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም፡፡

41|25|ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው፡፡ በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም

ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው፡፡ ከጋኔንና ከሰውም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር

ኾነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው፡፡ እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና፡፡

41|26|እነዚያም የካዱት «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ (ሲነበብ) በእርሱ

ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ፡፡

248

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!