26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

78|31|ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡

78|32|አትክልቶችና ወይኖችም፡፡

78|33|እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡

78|34|የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡

78|35|በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡

78|36|ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡

78|37|የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው

(ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡

78|38|መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን

ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡

78|39|ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡

78|40|እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው

ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡

ሱረቱ አል ናዚዓት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

79|1|በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤

79|2|በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤

79|3|መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤

79|4|መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤

79|5|ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

79|6|ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤

79|7|ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

79|8|በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡

79|9|ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡

79|10|«እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡

79|11|«የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)»

79|12|«ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡

79|13|እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡

79|14|ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡

79|15|የሙሳ ወሬ መጣልህን?

79|16|ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤

79|17|ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡

79|18|በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?»

79|19|«ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡

79|20|ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡

314

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!