26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

29|37|አስተባባሉትም፡፡ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ በሃገራቸውም ውስጥ ተንከፍርረው

አነጉ፡፡

29|38|ዓድንና ሰሙድንም (አጠፋን)፡፡ ከመኖሪያዎቻቸውም (ፍርስራሾች በኩል

መጥፋታቸው) ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ፡፡ ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ

ሸለመላቸው፡፡ ከመንገድም አገዳቸው፡፡ የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ፤ (ግን አላስተዋሉም)፡፡

29|39|ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም (አጠፋን)፡፡ ሙሳም በተዓምራቶች በእርግጥ

መጣባቸው፡፡ በምድርም ላይ ኮሩ፡፡ አምላጪዎችም አልነበሩም፡፡

29|40|ሁሉንም በኅጢኣቱ ያዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡

፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት

አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን

ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡

29|41|የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች

ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ

(አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡

29|42|አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚግገዙትን ማንኛውንም ያውቃል፡፡ እርሱም አሸናፊው

ጥበበኛው ነው፡፡

29|43|እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን፡፡ ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎቹ

አያውቋትም፡፡

29|44|«አላህ ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፡፡» በዚህ ውስጥ ለምእምናን

ተዓምር አለበት፡፡

29|45|ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡

ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ

ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡

29|46|የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡

ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው

አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡»

29|47|እንደዚሁም ወዳንተ መጽሐፍን አወረድን፡፡ እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው፤ በእርሱ

ያምናሉ፡፡ ከእነዚህም (ከመካ ሰዎች) በእርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ በተዓምራቶቻችንም ከሓዲዎቹ

እንጂ ማንም አይክድም፡፡

29|48|ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፡፡ ያን ጊዜ

አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡

29|49|አይደለም እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ ዕውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ

(የጠለቀ) ግልጾች አንቀጾች ነው፡፡ በአንቀጾቻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡

29|50|«በእርሱ ላይም ከጌታህ ዘንድ ተዓምራቶች ለምን አልተወረዱም» አሉ፡፡

«ተዓምራቶች አላህ ዘንድ ብቻ ናቸው፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ» በላቸው፡፡

29|51|እኛ መጽሐፉን በእነሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን

በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሳጼ አለበት፡፡

29|52|«በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለውን ሁሉ

ያውቃል» በላቸው፡፡ እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑ በአላህም የካዱ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎች

ናቸው፡፡

29|53|በቅጣትም ያስቸኩሉሃል፡፡ የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር፡፡

እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል፡፡

206

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!