26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

17|14|«መጽሐፍህን አንብብ፡፡ ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ» (ይባላል)፡፡

17|15|የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ)

በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ መልዕክተኛንም

እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡

17|16|ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ባለ ጸጋዎችዋን እናዛለን፡፡ በውስጧም ያምጻሉ፡፡

በእርሷም ላይ ቃሉ (ቅጣቱ) ይፈጸምባታል፡፡ ማጥፋትንም እናጠፋታለን፡፡

17|17|ከኑሕም በኋላ ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ የባሮቹንም

ኃጢኣቶች ውስጠ ዐዋቂ ተመልካች መኾን በጌታህ በቃ፡፡

17|18|ቸኳይቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሰው ለእርሱ በርሷ ውስጥ የሻነውን (ጸጋ)

ለምንሻው ሰው እናስቸኩልለታለን፡፡ ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን (መኖሪያ) አድርገንለታል፡፡

ተወቃሽ ብራሪ ኾኖ ይገባታል፡፡

17|19|መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው እርሱ አማኝ ኾኖ ለርሷ (ተገቢ) ሥራዋን

የሠራም ሰው እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይኾናል፡፡

17|20|ሁሉንም እነዚህንና እነዚያን ከጌታህ ስጦታ (በዚህ ዓለም) እንጨምርላቸዋለን፡፡

የጌታህም ስጦታ (በዚች ዓለም) ክልክል አይደለም፡፡

17|21|ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳበለጥን ተመልከት፡፡ የመጨረሻያቱም አገር

በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የተለቀች ናት፡፡

17|22|ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትኾናለህና፤

17|23|ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም

መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ

አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡

17|24|ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ

(በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡

17|25|ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ

(በመሳሳትም ብታጠፉ) እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው፡፡

17|26|ለዝምድና ባለቤትም መብቱን ስጥ፡፡ ለምስኪንና ለመንገደኛም (ስጥ)፡፡ ማባከንንም

አታባክን፡፡

17|27|አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፡፡ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

17|28|ከጌታህም የምትከጅላትን ጸጋ ለማጣት ከእነርሱ ብትዞር ለእነሱ ልዝብን ቃል

ተናገራቸው፡፡

17|29|እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤

የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና፡፡

17|30|ጌታህ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ እርሱ በባሮቹ ኹኔታ ውስጠ

ዐዋቂ ተመልካች ነውና፡፡

17|31|ልጆቻችሁንም ድኽነትን ለመፍራት አትግደሉ፡፡ እኛ እንመግባቸዋለን፡፡ እናንተንም

(እንመግባለን)፡፡ እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢኣት ነውና፡፡

17|32|ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!

17|33|ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ የተበደለም ኾኖ የተገደለ ሰው

ለዘመዱ (በገዳዩ ላይ) በእርግጥ ስልጣንን አድርገናል፡፡ በመግደልም ወሰንን አይለፍ፤ እርሱ

የተረዳ ነውና፡፡

142

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!