26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

12|83|(ያዕቆብ) «አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡

(ሠራችሁትም)፡፡ መልካምም ትእግስት (ማድረግ) አለብኝ፡፡ እነርሱን (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ

ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፡፡ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና» አላቸው፡፡

12|84|ከእነሱም ዘወር አለናኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ)

የተነሳ ነጡ፡፡ እርሱም በትካዜ የተመላ ነው፡፡

12|85|(እነርሱም) «በአላህ እንምላለን፡፡ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ

እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም» አሉ፡፡

12|86|«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል

የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡

12|87|«ልጆቼ ሆይ! ሊዱ፤ ከዩሱፍና ከወንድሙም (ወሬ) ተመራመሩ፡፡ ከአላህም እዝነት

ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲዎች ሕዝቦች እንጂ ተስፋ አይቆርጥም» (አለ)፡፡

12|88|በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት

ደረሰብን፡፡ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፡፡ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፡፡ በኛም ላይ መጽውት

አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና» አሉት፡፡

12|89|«እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሰራችሁትን ግፍ

ዐወቃችሁን» አላቸው፡፡

12|90|«አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን» አሉት፡፡ «እኔ ዩሱፍ ነኝ፡፡ ይህም ወንድሜ

ነው፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን፡፡ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው (አላህ

ይክሰዋል)፡፡ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና» አለ፡፡

12|91|«በአላህ እንምላለን፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፡፡ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች

ነበርን» አሉ፡፡

12|92|«ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም፡፡ አላህ ለእናንተ ይምራል፡፡ እርሱም ከአዛኞች

ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው» አላቸው፡፤

12|93|«ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሊዱ፡፡ በአባቴ ፊትም ጣሉት የሚያይ ሆኖ ይመጣልና፡፡

ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ» (አላቸው)፡፡

12|94|ግመል ጫኞቹም (ምስርን) በተለዩ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ

አገኛለሁ፡፡ ባታቄሉኝ ኖሮ (ታምኑኝ ነበር)» አለ፡፡

12|95|«በአላህ እንምላለን፡፡ አንተ በእርግጥ በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ» አሉት፡፡

12|96|አብሳሪውም በመጣ ጊዜ (ቀሚሱን) በፊቱ ላይ ጣለው፡፡ ወዲውም የሚያይ ኾነ፡፡

«እኔ ለእናንተ፡- ከአላህ በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን» አላቸው፡፡

12|97|«አባታችን ሆይ! ለኀጢአቶቻችን ምሕረትን ለምንልን እኛ ጥፋተኞች ነበርንና» አሉ፡፡

12|98|«ወደፊት ለእናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ፡፡ እነሆ! እርሱ መሓሪው

አዛኙ ነውና» አላቸው፡፤

12|99|በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደርሱ አስጠጋቸው፡፡ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች

ስትኾኑ ምስርን ግቡ» አላቸው፡፡

12|100|ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው ወረዱለት፡፡

«አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡

ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ከአበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር

ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለኔ መልካም ዋለልኝ፡፡ ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው፡፡

እነሆ እሱ ዐዋቂው ጥበበኛው ነው» አለ፡፡

122

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!