26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

15|74|ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡

15|75|በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡

15|76|እሷም (ከተማይቱ) በቀጥታ መንገድ ላይ ናት፡፡

15|77|በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለምእምናን መገሰጫ አለ፡፡

15|78|እነሆ የአይከት ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ፤

15|79|ከነሱም ተበቀልን ሁለቱም (የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች) በእርግጥ በግልጽ

መንገድ ላይ ናቸው፡፡

15|80|የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡

15|81|ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡

15|82|ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡

15|83|ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡

15|84|ይሠሩትም የነበሩት ሕንጻ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡

15|85|ሰማያትንና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ (በላግጣ)

አልፈጠርንም፡፡ ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት፡፡ መልካምንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡

15|86|ጌታህ እርሱ (ያልነበረን) ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡

15|87|ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡

15|88|ከእነርሱ (ከከሓዲዎች) ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን

አትዘርጋ፡፡ በእነሱም ላይ (ባያምኑ) አትዘን፡፡ ክንፍህንም ለምእምናን አለዝብ፡፡

15|89|በልም «እኔ ግልጽ አስፈራሪው እኔ ነኝ፡፡»

15|90|(ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (በኾነ ቅጣት

አሰፈራሪያችሁ ነኝ በል)፡፡

15|91|(እነርሱም) እነዚያ ቁርኣንንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው፡፡

15|92|በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤

15|93|ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡

15|94|የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡

15|95|ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡

15|96|(እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፡፡ በእርግጥም

(ፍጻሜያቸውን) ወደፊት ያውቃሉ፡፡

15|97|አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡

15|98|ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡

15|99|እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡

133

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!