26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

19|86|ከሓዲዎችንም የተጠሙ ኾነው ወደ ገሀነም የምንነዳበትን (ቀን አስታውስ)፡፡

19|87|አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡

19|88|«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡

19|89|ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡

19|90|ከእርሱ (ከንግግራቸው) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው

ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡

19|91|ለአልረሕማን ልጅ አልለው ስለአሉ፡፡

19|92|ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡

19|93|በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው

የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡

19|94|በእርግጥ (በዕውቀቱ) ከቧቸዋል፡፡ መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል፡፡

19|95|ሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡

19|96|እነዚያ ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ አልረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል፡፡

19|97|በምላስህም (ቁርኣንን) ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በእርሱም

ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስፈራራበት ነው፡፡

19|98|ከእነሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን አጥፍተናል፡፡ ከእነሱ አንድን

እንኳ ታያለህን ወይስ ለእነሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን

ሱረቱ ጣሃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

20|1|ጠ.ሀ. (ጣ ሃ)

20|2|ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡

20|3|ግን አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ ይኾን ዘንድ (አወረድነው)፡፡

20|4|ምድርንና የላይኛዎቹን ሰማያት ከፈጠረ አምላክ ተወረደ፡፡

20|5|(እርሱ) አልረሕማን ነው በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡

20|6|በሰማያት ያለው፣ በምድርም ያለው፣ በመካከላቸውም ያለው፣ ከዐፈር በታችም ያለው

ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡

20|7|በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው)፡፡ እርሱ ምስጢርን በጣም

የተደበቀንም ያውቃልና፡፡

20|8|አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አልሉት፡፡

20|9|የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡

20|10|እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ፡- (እዚህ) «ቆዩ፤ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ችቦን

ላመጣላችሁ፤ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ» ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡

20|11|በመጣትም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡

157

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!