26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

8|30|እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ

በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም

ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡

8|31|አንቀጾቻችንም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ

ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡

8|32|«ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ (የተወረደ) እውነት እንደ ኾነ በኛ ላይ

ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን» ባሉም ጊዜ (አስታውስ)

8|33|አላህም አንተ በውስጣቸው እያለህ (ድንጋይ በማዝነብና ባሳማሚ ቅጣት)

የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡

8|34|እነሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲኾኑም አላህ (በሰይፍ) የማይቀጣቸው ለነሱ

ምን አልላቸው (የቤቱ) ጠባቂዎችም አልነበሩም፡፡ ጠባቂዎቹ (ክሕደትን) ተጠንቃቂዎቹ እንጂ

ሌሎቹ አይደሉም፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡

8|35|በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡

ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡

8|36|እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ፡፡ በእርግጥም

ያወጡዋታል፡፡ ከዚያም በእነሱ ላይ ጸጸት ትኾንባቸዋለች፡፡ ከዚያም ይሸነፋሉ፡፡ እነዚያም የካዱት

ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ፡፡

8|37|አላህ መጥፎውን ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና

ባንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ)፡፡ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ

ናቸው፡፡

8|38|ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት

ይደረግላቸዋል፡፡ (ወደ መጋደል) ቢመለሱም (እናጠፋቸዋለን)፡፡ የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ

በእርግጥ አልፋለችና፡፡

8|39|ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡

ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

8|40|(ከእምነት) ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መኾኑን ዕወቁ፡፡ (እርሱ) ምን ያምር ጠባቂ!

ምን ያምርም ረዳት!

8|41|ከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የዘረፋችሁትም አንድ አምስተኛው ለአላህና

ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም

የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች

በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን

ዕወቁ)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

8|42|እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ኾናችሁ እነርሱም በሩቂቱ ዳርቻ ኾነው የነጋዴዎቹም ጭፍራ

ከናንተ በታች ሲኾኑ በሰፈራችሁ ጊዜ (ያደረግንላችሁን አስታውሱ)፡፡ በተቃጠራችሁም ኖሮ

በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው

ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን (ያለቀጠሮ

አጋጠማችሁ)፡፡ አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

8|43|አላህ በሕልምህ እነሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ እነሱን ብዙ አድርጎ

ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ አዳናችሁ፡፡ እርሱ

በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡

90

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!