26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚያ (መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ

ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው፡፡

24|27|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ

ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ትገነዘቡ

ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡

24|28|በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት፡፡

ለእናንተ ተመለሱ ብትባሉም ተመለሱ፡፡ እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን

ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

24|29|መኖሪያ ያልኾኑን ቤቶች በውስጣቸው ለእናንተ ጥቅም ያላችሁን (ሳታስፈቅዱ)

ብትገቡ በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ አላህም የምትገልጹትንና የምትደብቁትን ሁሉ

ያውቃል፡፡

24|30|ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤

ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡

24|31|ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡

ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው

ላይ ያጣፉ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው

አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም

ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች

ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ

የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ

በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡

ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡

24|32|ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም

ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም

ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡

24|33|እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ

ይጠበቁ፡፡ እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች (ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት)

መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነሱ መልካምን ነገር ብታውቁ ተጻጻፉዋቸው፡፡ ከአላህም ገንዘብ ከዚያ

ከሰጣችሁ ስጧቸው፡፡ ሴቶች ባሮቻችሁንም መጥጠበቅን ቢፈልጉ የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም

ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ላይ አታስገድዱዋቸው፡፡ የሚያስገድዳቸውም ሰው አላህ

ከመገደዳቸው በኋላ (ለተገደዱት) መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

24|34|ወደእናንተም አብራሪ የኾኑን አንቀጾች ከእነዚያ ከበፊታችሁ ካለፉትም (ምሳሌዎች

ዓይነት) ምሳሌን ለጥንቁቆቹ መገሰጫንም በእርግጥ አወረድን፡፡

24|35|አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት

(ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ

የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት

ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡

፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡

አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

24|36|አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)፡፡

በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡

180

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!