26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

ዘንድ ከአላህ የኾነችን ምስክርነት ከደበቀ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? አላህም ከምትሠሩት

ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡

2|141|ይህቺ በእርግጥ ያለፈች ሕዝብ ናት፤ ለእርሷ የሠራችው አላት፤ ለናንተም የሠራችሁት

አላችሁ፤ ይሠሩትም ከነበሩት አትጠየቁም፡፡

2|142|ከሰዎቹ ቂሎቹ «ከዚያች በርሷ ላይ ከነበሩባት ቂብላቸው ምን አዞራቸው?» ይላሉ፤

«ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው፤ የሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል»

በላቸው፡፡

2|143|እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልክተኛውም

በናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ ምርጥ ሕዝቦች አደረግናችሁ፡፡ ያችንም በርሷ ላይ

የነበርክባትን አቅጣጫ መልክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው

ልናውቅ (ልንገልጽ) እንጅ ቂብላ አላደረግናትም፡፡ እርሷም በነዚያ አላህ በመራቸው ሰዎች ላይ

በስተቀር በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) የሚያጠፋ አይደለም፤

አላህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡

2|144|የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ

እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም

ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡ እነዚያም መጽሐፉን

የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት መሆኑን ያውቃሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ

አይደለም፡፡

2|145|እነዚያንም መጽሐፍን የተሰጡትን በአስረጅ ሁሉ ብትመጣቸው ቂብላህን አይከተሉም፡፡

አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም፡፡ ከፊላቸውም የከፊሉን ቂብላ ተከታይ አይደሉም፡፡

ከዕውቀትም (ከራዕይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተ ያን ጊዜ ከበዳዮች

ነህ፡፡

2|146|እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን)

ያውቁታል፡፡ ከነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፡፡

2|147|(ይህ) ከጌታህ የኾነ እውነት ነው፤ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡

2|148|ለሁሉም እርሱ (በስግደት ፊቱን) የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው፡፡ ወደ መልካም

ሥራዎችም ተሽቀዳደሙ፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑ አላህ እናንተን የተሰበሰባችሁ ኾናችሁ

ያመጣችኋል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡

2|149|ከየትም (ለጉዞ) ከወጣህበት ስፍራ ፊትሀን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡

፡ እርሱም ከጌታህ የኾነ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ አይደለም፡፡

2|150|ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡ በየትም

ስፍራ ብትኾኑ ለሰዎቹ እነዚያ ከነሱ የበደሉት ሲቀሩ (ሃይማኖታችንን ይክዳሉ ቂብላችንን

ይከተላሉ በማለት) በናንተ ላይ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው ፊቶቻችሁን ወደ አግጣጫው

አዙሩ፡፡ አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም፤ (በዚህም ያዘዝኳችሁ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው) በናንተም

ላይ ጸጋየን እንድሞላላችሁና (ወደ እውነትም) እንድትመሩ ነው፡፡

2|151|በውስጣችሁ ከናንተው የኾነን በናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና

የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር

የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን (ጸጋን ሞላንላችሁ)፡፡

2|152|አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡

2|153|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች

ጋር ነውና፡፡

16

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!