26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

4|106|አላህንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

4|107|ከእነዚያም ነፍሶቻቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር፡፡ አላህ ከዳተኛ ኃጢአተኛ

የኾነን ሰው አይወድምና፡፡

4|108|ከሰው ይደበቃሉ፡፡ አላህም እርሱ (በዕውቀቱ) ከእነሱ ጋር ሲኾን ከንግግር

የማይወደውን ነገር (በልቦቻቸው) በሚያሳድሩ ጊዜ (ከእርሱ) አይደበቁም፡፡ አላህም በሚሠሩት

ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡

4|109|እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ከነሱ የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ በትንሣኤ ቀን

አላህን ስለእነሱ የሚከራከር ማን ነው ወይስ ለእነሱ ኃላፊና መመኪያ የሚኾን ማን ነው

4|110|መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይም ነፍሱን የሚበድል ከዚያም (ተጸጽቶ) አላህን

ምሕረት የሚለምን አላህን መሓሪ አዛኝ ኾኖ ያገኘዋል፡፡

4|111|ኀጢአትንም የሚሠራ ሰው የሚሠራው ጥፋት በራሱ ላይ ነው፡፡ አላህም ዐዋቂ

ጥበበኛ ነው፤

4|112|ኀጢአትን ወይም አበሳን የሚሠራም ሰው ከዚያም በእርሱ ንጹሕን ሰው የሚሰድብ

ቅጥፈትንና ግልጽ አበሳን በቁርጥ ተሸከመ፡፡

4|113|የአላህም ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነሱ የኾኑ ጭፍሮች ሊያሳስቱህ

ባሰቡ ነበር፡፡ ነፍሶቻቸውንም እንጅ ሌላን አያሳስቱም፡፡ በምንም አይጐዱህም፡፡ አላህም በአንተ

ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ

ላይ ታላቅ ነው፡፡

4|114|ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ

ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም

(የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡

4|115|ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ

መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤

ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!

4|116|አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው

ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡

4|117|ከእርሱ ሌላ እንስታትን እንጅ አይገዙም፡፡ አመጸኛ ሰይጣንንም እንጅ ሌላን

አይግገዙም፡፡

4|118|«አላህ የረገመውን ከባሮችህም የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ» ያለውን

(ሰይጣን እንጅ ሌላን አይከተሉም)፡፡

4|119|በእርግጥ አጠማቸዋለሁም፡፡ (ከንቱን) አስመኛቸዋለሁም፡፡ አዛቸውምና የእንስሶችን

ጆሮዎች ይተለትላሉ፡፡ አዛቸውምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ፤ (ያለውን ይከተላሉ)፡፡

ከአላህም ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ሰው ግልጽ ክስረትን በአርግጥ ከሰረ፡፡

4|120|(የማይፈጸመውን) ተስፋ ይሰጣቸዋል፡፡ ያስመኛቸዋልም፡፡ ሰይጣንም ለማታለል እንጅ

አይቀጥራቸውም፡፡

4|121|እነዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ ከርስዋም መሸሻን አያገኙም፡፡

4|122|እነዚያም ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች

ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ እናገባቸዋለን፡፡ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው፡፡

በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው

4|123|(ነገሩ) በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም፡፡ መጥፎን የሚሠራ ሰው

በእርሱ ይቀጣል፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂንም ረዳትንም አያገኝም፡፡

49

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!