26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

74|43|(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡

74|44|«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡

74|45|«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡

74|46|«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡

74|47|«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡»

74|48|የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡

74|49|ከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው?

74|50|እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡

74|51|ከዐንበሳ የሸሹ፡፡

74|52|ይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡

74|53|ይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡

74|54|ይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡

74|55|ስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡

74|56|አላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም

ባለቤት ነው፡፡

ሱረቱ አል ቂያማህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

75|1|(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡

75|2|(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

75|3|ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?

75|4|አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን

(እንሰበስባቸዋለን)፡፡

75|5|ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡

75|6|«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡

75|7|ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡

75|8|ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡

75|9|ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡

75|10|«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡

75|11|ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡

75|12|በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

75|13|ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡

75|14|በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡

75|15|ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡

75|16|በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡

75|17|(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡

75|18|ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡

75|19|ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡

309

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!