26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

6|82|እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡

እነሱም የተመሩ ናቸው፤

6|83|ይህችም ማስረጃችን ናት፡፡ ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ (አስረጅ እንድትኾን) ሰጠናት፡፡

የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡

6|84|ለርሱም ኢስሐቅን (የልጅ ልጁን) ያዕቁብንም ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መራን፡፡ ኑሕንም

በፊት መራን፡፡ ከዘሮቹም ዳውድን፣ ሱለይማንንም፣ አዩብንም፣ ዩሱፍንም፣ ሙሳንም፣ ሃሩንንም

(መራን)፡፡ እንደዚሁም በጎ ሰሪዎችን እንመነዳለን፡፡

6|85|ዘከሪያንም፣ የሕያንም፣ ዒሳንም፣ ኢልያስንም (መራን)፡፡ ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡

6|86|ኢስማዒልንም፣ አልየስዕንም፣ ዩኑስንም፣ ሉጥንም (መራን)፡፡ ሁሉንም በዓለማት ላይ

አበለጥናቸውም፡፡

6|87|ከአባቶቻቸውም፣ ከዘሮቻቸውም፣ ከወንድሞቻቸውም (መራን)፡፡ መረጥናቸውም፤ ወደ

ቀጥታውም መንገድ መራናቸው፡፡

6|88|ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ ባጋሩም ኖሮ

ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡

6|89|እነዚህ እነዚያ መጻሕፍትንና ጥበብን፣ ነቢይነትንም የሰጠናቸው ናቸው፡፡ እነዚህ (የመካ

ከሓዲዎች) በእርሷ ቢክዱም በእርሷ የማይክዱን ሕዝቦች ለእርሷ በእርግጥ አዘጋጅተናል፡፡

6|90|እነዚህ (ነቢያት)፤ እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው፡፡ በመንገዳቸውም ተከተል፡፡

«በእርሱ (በቁርአን) ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ እርሱ ለዓለማት ግሣጼ እንጅ ሌላ

አይደለም» በላቸው፡፡

6|91|«አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም» ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን

አላከበሩትም፡፡ (እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን

መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ

ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤»

6|92|«አላህ (አወረደው)» በላቸው፡፡ ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲኾኑ

ተዋቸው፡፡ ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ ያንንም በፊቱ የነበረውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ

መጽሐፍ ነው፡፡ የከተሞችን እናት (መካን) እና በዙሪያዋ ያሉትንም ሰዎች ልታስጠነቅቅበት

(አወረድነው)፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያምኑት እነርሱ በሶላታቸው ላይ

የሚጠባበቁ ሲኾኑ በርሱ ያምናሉ፡፡

6|93|በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲኾን «ወደኔ

ተወረደልኝ» ካለና፡-«አላህም ያወረደውን ብጤ በእርግጥ አወርዳለሁ» ካለ ሰው ይበልጥ በዳይ

ማን ነው በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች

ኾነው « (ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ በአላህ ላይ እውነት ያልኾነን ነገር ትናገሩ

በነበራችሁትና ከአንቀጾቹም ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ»

(የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡

6|94|መጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ

የተዋችሁ ስትኾኑ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ

በእርግጥ መጣችሁን እነዚያንም እነሱ በእናንተ ውስጥ (ለአላህ) ተጋሪዎች ናቸው

የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፡፡ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡

ከእናንተም ያ (ያማልደናል) የምትሉት ጠፋ (ይባላሉ)፡፡

69

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!