26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

38|53|ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተሰፋ ነው፡፡

38|54|ይህ ሲሳያችን ነው፡፡ ለእርሱ ምንም ማለቅ የለውም፡፡

38|55|ይህ (ለአማኞች ነው)፡፡ ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው፡፡

38|56|የሚገቧት ስትኾን ገሀነም (አለቻቸው)፡፡ ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች፡፡

38|57|ይህ (ለከሓዲዎች ነው)፡፡ ይቅመሱትም፡፡ የፈላ ውሃና እዥ ነው፡፡

38|58|ሌላም ከመሰሉ ዓይነቶች አልሉ፡፡

38|59|ይህ ከእናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ጭፍራ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ለእነርሱ አይስፋቸው፡፡

እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)፡፡

38|60|(ተከታዮቹ) ይላሉ «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ፡፡ እናንተ (ክህደቱን) ለእኛ

አቀረባችሁት፡፡ መርጊያይቱም (ገሀነም) ከፋች፡፡»

38|61|«ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ እጥፍን ቅጣት ጨምርለት»

ይላሉ፡፡

38|62|ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች (እዚህ)

አናይምሳ፡፡»

38|63|«መቀለጃ አድርገን ያዝናቸውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነሱ ዋለሉ?»

38|64|ይህ በእርግጥ እምነት ነው፡፡ (እርሱም) የእሳት ሰዎች (የእርስ በእርስ) መካሰስ

ነው፡፡

38|65|«እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ፡፡ ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም»

በላቸው፡፡

38|66|«የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡»

38|67|በላቸው «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው፡፡

38|68|«እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡

38|69|(በአደም ነገር) «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት

አልነበረኝም፡፡

38|70|«ወደእኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝም» (በል)፡፡

38|71|ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» (አስታውስ)፡፡

38|72|«ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ

ውደቁ» (አልኩ)፡፡

38|73|መላእክትም መላውም ባንድነት ሰገዱ፡፡

38|74|ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ኮራ፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡

38|75|(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን

ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡

38|76|«እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ ከጭቃም ፈጠርከው» አለ፡፡

38|77|(አላህ) አለው «ከእርሷ ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና፡፡»

38|78|«እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን፡፡»

38|79|«ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝም» አለ፡፡

38|80|(አላህም) አለው «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡»

38|81|«እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡»

38|82|(እርሱም) አለ «በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡»

38|83|«ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡»

38|84|(አላህ) አለው «እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡

237

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!