26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

3|129|በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፤

የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

3|130|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲኾኑ አትብሉ፡፡ ትድኑም ዘንድ

አላህን ፍሩ፡፡

3|131|ያችንም ለከሓዲዎች የተደገሰችውን እሳት ተጠንቀቁ፡፡

3|132|ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡

3|133|ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት

አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡

3|134|ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ

አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡

3|135|ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን

የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን

የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ

ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡

3|136|እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው

ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች!፡፡

3|137|ከእናንተ በፊት ድርጊቶች በእርግጥ አልፈዋል፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ፡፡

የአስተባባዮችም ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡

3|138|ይህ ለሰዎች ገላጭ፤ ለጥንቁቆች መሪና ገሳጭ ነው፡፡

3|139|እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡

3|140|ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ ይኽችንም ቀናት በሰዎች

መካከል እናዘዋውራታለን፡፡ (እንድትገሰጹና) አላህም እነዚያን ያመኑትን እንዲያውቅ (እንዲለይ)

ከእናንተም ሰማዕታትን እንዲይዝ ነው፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡

3|141|አላህም እነዚያን ያመኑትን (ከኀጢአት) ሊያነጻና ከሓዲዎችንም ሊያጠፋ ነው፡፡

3|142|በእውነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያውቅ

ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን

3|143|(በጦርነት ላይ) መሞትንም ሳታገኙት በፊት በርግጥ የምትመኙት ነበራችሁ፡፡

እናንተም የምትመለከቱ ስትኾኑ በርግጥ አያችሁት (ታዲያ ለምን ሸሻችሁ)

3|144|ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ

አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደኋላው የሚገለበጥም

ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡

3|145|ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢኾን እንጅ ልትሞት አይገባትም፡፡ (ጊዜውም)

ተወስኖ ተጽፏል፡፡ የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፡፡ የመጨረሻይቱንም

ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን፡፡

3|146|ከነቢይም ብዙ ሊቃውንት ከርሱ ጋር ኾነው የተዋጉ ብዙ ናቸው፡፡ በአላህም መንገድ

ለሚደርስባቸው ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፡፡ (ለጠላት) አልተዋረዱምም፡፡ አላህም

ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡

3|147|ንግግራቸውም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን

ለእኛ ማር፣ ይዞታችንንም አደላድል፣ በከሓዲዎችም ሕዝቦች ላይ እርዳን» ማለታቸው እንጅ

ሌላ አልነበረም፡፡

36

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!