26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

28|55|ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ፡፡ «ለእኛ ሥራዎቻችን አሉን፡፡ ለናንተም

ሥራዎቻችሁ አሏችሁ፡፡ ሰላም በእናንተ ላይ (ይኹን) ባለጌዎችን አንፈልግም» ይላሉ፡፡

28|56|አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል

እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡

28|57|«ከአንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን» አሉም፡፡ ከእኛ ዘንድ

(የተሰጠ) ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደእርሱ የሚነዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን)

ለእነሱ አላስመቸናቸውምን ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

28|58|ከከተማም ኑሮዋን (ምቾቷን) የካደችን (ከተማ) ያጠፋናት ብዙ ናት፡፡ እነዚህም

ከእነሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጅ ያልተኖረባቸው ሲኾኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው፡፡ እኛም

(ከእነርሱ) ወራሾች ነበርን፡፡

28|59|ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ (ከተማ) ውስጥ አንቀጾቻችንን በእነሱ ላይ የሚያነብ

መልክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም፡፡ ከተሞችንም ባለቤቶቿ በዳዮች ሆነው እንጅ

አጥፊዎች አልነበርንም፡፡

28|60|ከማንኛውም ነገር የተሰጣችሁት፤ የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅምና ጌጧ ነው፡፡ አላህ ዘንድ

ያለውም (ምንዳ) በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው አታውቁምን

28|61|መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት

ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያም እርሱ በትንሣኤ ቀን (ለእሳት) ከሚቀረቡት እንደ ኾነው ሰው

ነውን

28|62|(አላህ) የሚጠራባቸውንና እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው

የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡

28|63|እነዚያ በእነርሱ ላይ ቃሉ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ እነዚያ

ያጠመምናቸው ናቸው፡፡ እንደጠመምን አጠመምናቸው፡፡ (ከእነሱ) ወዳንተ ተጥራራን፡፡ እኛን

ይግገዙ አልነበሩም፡፡

28|64|«(ለአላህ) የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ፤ ይጠሯቸዋልም፡፡ ግን ለእነርሱ

አይመልሱላቸውም፡፡ ቅጣቱንም ያያሉ፡፡ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር)፡፡

28|65|«የሚጠራባቸውንና ለመልክተኞቹም ምንን መለሳችሁ» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡

28|66|በዚያም ቀን ወሬዎቹ ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰውሩባቸዋል፡፡ እነርሱም አይጠያየቁም፡፡

28|67|የተጸጸተና ያመነ ሰውማ መልካምንም የሠራ ከሚድኑት ሊኾን ይከጀላል፡፡

28|68|ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ (ለሰዎቹ) ምርጫ የላቸውም፡

፡ አላህ ከማይግገባው ሁሉ ጠራ፡፡ ከሚያጋሯቸውም ላቀ፡፡

28|69|ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡

28|70|እርሱም አላህ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ምስጋና በመጀመሪያይቱም

በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም

ትመለሳላችሁ፡፡

28|71|አያችሁን (ንገሩኝ) «አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ

ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው አትሰሙምን» በላቸው፡፡

28|72|አያችሁን «አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው

ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው (ንገሩኝ)

አታስተውሉምን» በላቸው፡፡

202

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!