26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

25|11|ይልቁንም በትንሣኤ አስተባበሉ፡፡ በትንሣኤ ላስተባበለም ሰው ሁሉ ነዳጅን እሳት

አዘጋጅተናል፡፡

25|12|ከሩቅ ስፍራ ባየቻቸው ጊዜ ለእርሷ የቁጭት መገንፈልንና ማናፋትን ይሰማሉ፡፡

25|13|እጅ ከፍንጅ የታሠሩ ኾነውም ከእርሷ በጠባብ ስፍራ በተጣሉ ጊዜ በዚያ ስፍራ

ጥፋትን ይጠራሉ፤ (ዋ ጥፋታችን ይላሉ)፡፡

25|14|፡-ዛሬ አንድን ጥፋት ብቻ አትጥሩ ብዙንም ጥፋት ጥሩ (ይባላሉ)፡፡

25|15|(እንዲህ) በላቸው «ይህ የተሻለ ነውን ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ

ገነት» ለእነርሱ ምንዳና መመለሻ ኾነች፡፡

25|16|ለእነሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው የሚፈልጉት ሁሉ አልላቸው፡፡ (ይህም) ተስፋ

ከጌታህ ተለማኝ ተስፋ ነው፡፡

25|17|እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸውንም የሚሰበስብባቸውንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን

አሳሳታችሁን ወይስ እነሱው መንገድን ሳቱ» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡

25|18|«ጥራት ይገባህ፤ ካንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ ለእኛ ተገቢያችን አልነበረም፡፡ ግን

እነርሱንም አባቶቻቸውንም መገንዘብን እስከተዉ ድረስ አጣቀምካቸው፡፡ ጠፊ ሕዝቦችም ኾኑ»

ይላሉ፡፡

25|19|በምትሉትም (አማልክቶቻችሁ) አስዋሹዋችሁ፡፡ ቅጣቴን መገፍተርንም መርዳትንም

አትችሉም፡፡ ከእናንተም የሚበድለውን ታላቅን ቅጣት እናቀምሰዋለን፤ (ይባላሉ)፡፡

25|20|ከአንተ በፊትም ከመልክተኞች እነሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ

ኾነው በስተቀር አልላክንም፡፡ ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል፡፡ ትታገሳላችሁን ጌታህም

ተመልካች ነው፡፡

25|21|እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም፡፡ ወይም

ጌታችንን ለምን አናይም አሉ፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ፡፡

25|22|መላእክትን በሚያዩበት ቀን በዚያ ጊዜ ለአመጸኞች ምስራች የላቸውም፡፡ «የተከለከለ

ክልክልም አድርገን» ይላሉ፡፡

25|23|ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን፡፡

25|24|የገነት ሰዎች በዚያ ቀን በመርጊያ የተሻሉ በማረፊያም በጣም ያማሩ ናቸው፡፡

25|25|ሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መወረድን የሚወርድበትን ቀን

(አስታውስ)፡፡

25|26|እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው፡፡ በከሓዲዎችም ላይ

አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡

25|27|በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ

(በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡

25|28|«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡

25|29|(የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)፡፡

ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡

25|30|መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት»

አለ፡፡

25|31|እንደዚሁም ለነቢዩ ሁሉ ከአመጸኞች የኾነ ጠላትን አድርገናል፡፡ መሪና ረዳትም

በጌታህ በቃ፡፡

184

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!