26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

56|90|ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡

56|91|ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡

56|92|ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡

56|93|ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡

56|94|በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡

56|95|ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡

56|96|የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡

ሱረቱ አል ሐዲድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

57|1|በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው

ነው፡፡

57|2|የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡

እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

57|3|እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ

ነው፡፡

57|4|እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ

(ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም

የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር

ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

57|5|የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ

ይመለሳሉ፡፡

57|6|ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፡፡ እርሱም በልቦች

ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነወ፡፡

57|7|በአላህና በመልክተኛው እመኑ፡፡ (አላህ) በእርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ

ለግሱ፡፡ እነዚያም ከእናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡

57|8|መልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲኾን (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም

የያዘባችሁ ሲኾን በአላህ የማታምኑት ለእናንተ ምን አልላችሁ? የምታምኑ ብትኾኑ

(ወደ እምነት ቸኩሉ)፡፡

57|9|እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የኾኑን አንቀጾች በበሪያው

ላይ የሚያወርድ ነው፡፡ አላህም ለእናንተ በእርግጥ ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡

57|10|የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ሲኾን በአላህ መንገድ የማትለግሱትም ለእናንተ ምን

አልላችሁ? ከእናንተ ውስጥ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው (ከተከፈተች

በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይስተካከልም፡፡ ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ

በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህም

በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

285

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!