26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

16|18|የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

16|19|አላህም የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡

16|20|እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ፤

16|21|ሕያው ያልኾኑ ሙታን ናቸው፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም፡፡

16|22|አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት

ልቦቻቸው ከሓዲዎች ናቸው፡፡ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም)፡፡

16|23|አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመኾኑ ጥርጣሬ የለበትም፡፡

እርሱ ኩሩዎችን አይወድም፡፡

16|24|ለእነርሱም «ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ» በተባሉ ጊዜ «(እርሱ)

የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው» ይላሉ፡፡

16|25|(ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ ከእነዚያም ያለ ዕውቀት

ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት

ምንኛ ከፋ!

16|26|እነዚያ ከእነሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አላህም

ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፡፡ ጣሪያውም በእነሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፡፡

ቅጣቱም ከማያውቁት ሥፍራ መጣባቸው፡፡

16|27|ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፡፡ እነዚያም «በእነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ

የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው» ይላቸዋል፡፡ «እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት ዛሬ ሐፍረቱና

ቅጣቱ በእርግጥ በከሓዲዎች ላይ ነው» ይላሉ፡፡

16|28|(እነርሱ) «እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ኾነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፡፡

ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን» (ሲሉ) ታዛዥነታቸውን ይገልጻሉ፡፡

«በእውነት አላህ ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው» (ይባላሉ)፡፡

16|29|«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ የኩሩዎችም

መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች!

16|30|ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር»

አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም

አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!

16|31|(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትኾን የመኖሪያ አትክልቶች

ናት፡፡ ለእነሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል፡፡

16|32|እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ

የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» (ይባላሉ)፡፡

16|33|(ከሓዲዎች) መላእክት ወደ እነሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን

እንጂ አይጠባበቁም፡፡ ከእነሱ በፊት የነበሩት እንደዚህ ሠርተዋል፡፡ አላህም አልበደላቸውም፤ ግን

ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡

16|34|የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች (ቅጣት) አገኛቸው፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ሁሉ

በነሱ ላይ ወረደባቸው፡፡

16|35|እነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም

ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለእርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፡፡»

እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት እነደዚሁ ሠሩ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ግልፅ ማድረስ ብቻ እንጂ

ሌላ የለባቸውም፡፡

135

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!