26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

10|41|«ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ

ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡

10|42|ከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ፡፡ አንተ ደንቆሮዎችን

የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን

10|43|ከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ፡፡ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም

ትመራለህን

10|44|አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡

10|45|(ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው

የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት

በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም፡፡

10|46|የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡

ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ

ላይ ዐዋቂ ነው፡፡

10|47|ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው፡፡ መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ)

በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡

10|48|«እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡

10|49|«ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ

የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም»

በላቸው፡፡

10|50|«ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር

ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው፡፡

10|51|«ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ

የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)፡፡

10|52|ከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ

እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ፡፡

10|53|እርሱም «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ

እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡

10|54|ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት

ነበር፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም

አይበደሉም፡፡

10|55|ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል

እርግጥ ነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

10|56|እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡

10|57|እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር

በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡

10|58|«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ

ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡

10|59|«አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን

አያችሁን» በላቸው፡፡ «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ

ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው፡፡

105

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!