26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

7|81|«እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ፡፡ በእውነቱ

እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ፡፡»

7|82|የሕዝቦቹም መልስ « (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው፡፡ እነሱ

የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡

7|83|እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት

ኾነች፡፡

7|84|በእነሱም ላይ (የእሳት) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት

እንደነበረ ተመልከት፡፡

7|85|ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው፡- «ወገኖቼ

ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ

በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን)

አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ

ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡»

7|86|« (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ

መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ፡፡ ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ

ጊዜ አስታውሱ፡፡ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡»

7|87|«ከእናንተም በዚያ እኔ በእርሱ በተላክሁበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም

ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሱ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡»

7|88|ከሕዝቦቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች፡- «ሹዓይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ከአንተጋር

ያመኑትን ከከተማችን በእርግጥ እናስወጣችኋለን፡፡ ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ

አሉ፡፡ የጠላንም ብንኾን» አላቸው፡፡

7|89|«አላህ ከእርሷ ከአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ

ውሸትን ቀጠፍን፡፡ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለእኛ ወደእርሷ ልንመለስ አይገባንም፡፡

ጌታችን ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ፡፡ በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን

መካከል በውነት ፍረድ፡፡ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ» (አለ)

7|90|ከወገኖቹም እነዚያ የካዱት መሪዎች «ሹዓይብን ብትከተሉ እናንተ ያን ጊዜ ከሳሪዎች

ናችሁ» አሉ፡፡

7|91|ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በከተማቸውም ውስጥ

ተንከፍርረው አነጉ፡፡

7|92|እነዚያ ሹዓይብን ያሰተባበሉት በእርሷ እንዳልነበሩባት ኾኑ፡፡ እነዚ ሹዓይብን

ያስተባበሉት እነርሱ ከሳሪዎች ኾኑ፡፡

7|93|ከእነርሱም (ትቷቸው) ዞረ፡- «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክቶች በእርግጥ

አደረስኩላችሁ፡፡ ለእናንተም መከርኩ፡፡ ታዲያ በከሓዲዎች ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ»

አለም፡፡

7|94|በከተማ አንድንም ነቢይ አልላክንም ሰዎችዋን ይዋደቁ ዘንድ በድህነትና በጉዳት

የያዝናቸው ብንኾን እንጂ፡፡

7|95|ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ

ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ

የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡

7|96|የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም

በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡

80

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!