26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

46|26|በዚያም እናንተን በእርሱ ባላስመቸንበት (ድሎት) በእርግጥ አስመቸናቸው፡፡

ለእነርሱም መስሚያንና ማያዎችን፣ ልቦችንም አደረግንላቸው፡፡ ግን መስሚያቸውና ማያዎቻቸው፣

ልቦቻቸውም ከእነሱ ምንም አልጠቀሟቸውም፡፡ በአላህ አንቀጾች ይክዱ ነበሩና፡፡ በእነርሱም ላይ

ያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ወረደባቸው፡፡

46|27|ከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ አጠፋን (ከክሕደታቸው)

ይመለሱም ዘንድ አስረጂዎችን መላለስን፡፡

46|28|እነዚያም መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የያዙዋቸው

አይረዷቸውም ኖሯልን? በእርግጥ ከነሱ ራቁ፡፡ ይህም ውሸታቸውና (በልማድ) ይቀጥፉት

የነበሩት ነው፡፡

46|29|ከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቁርኣንን የሚያዳምጡ ሲኾኑ ወዳንተ ባዞርን ጊዜም

(አስታውስ)፡፡ በተጣዱትም ጊዜ ዝም ብላችሁ አዳምጡ ተባባሉ፡፡ በተጨረሰም ጊዜ

አስጠንቃቂዎች ኾነው ወደ ሕዝቦቻቸው ተመለሱ፡፡

46|30|አሉም «ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ በፊቱ ያለውን

(መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የኾነን ሰማን፡፡

46|31|ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ (አላህ)

ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና፡፡

46|32|የአላህንም ጠሪ የማይቀበል ሰው በምድር ውስጥ የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ከእርሱም

ሌላ ለእርሱ ረዳቶች የሉትም፡፡ እነዚያ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ናቸው» (አሉ)፡፡

46|33|ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን

ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? (በማስነሳት) ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ

ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡

46|34|እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?»

(ይባላሉ)፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ (አላህም) «ትክዱ በነበራችሁት

ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል፡፡

46|35|ከመልክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡ ለእነርሱም

(ለሕዝቦችህ ቅጣት) አትቻኮል፡፡ ያንን የሚስፈራሩበትን ቅጣት በሚያዩ ቀን እነርሱ ከቀን

አንዲትን ሰዓት አንጅ እንዳልቆዩ ይኾናሉ፡፡ (ይህ ቁርኣን) በቂ ግሳጼ ነው አመጸኞችም

ሕዝቦች እንጅ (ሌሎች) ይጥጠፋሉን?

ሱረቱ አል ሙሃመድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

47|1|እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው፡፡

47|2|እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው

ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ

ያበጃል፡፡

47|3|ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመኾናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው

የኾነን እውነት ስለተከተሉ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል፡፡

264

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!