26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

34|17|በመካዳቸው ይህንን መነዳናቸው፤ (እንዲህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲን እንጂ

ሌላውን እንቀጣለን?

34|18|በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም

ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም

በቀኖችም ተጓዙ፤» (አልን)፡፡

34|19|«ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም በደሉ፡፡

(መገረሚያ) ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ

በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሰጫዎች አሉበት፡፡

34|20|ኢብሊስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ፤ ከአመኑትም የሆኑት ጭፍሮች

በስተቀር ተከተሉት፡፡

34|21|በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ

ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጅ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረውም፡፡

ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡

34|22|«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም

በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ

ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡

34|23|ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡

ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡

(አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡

34|24|«ከሰማያትና ከምድር (ዝናብንና በቃይን) የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው፡፡ «አላህ

ነው፡፡ እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን»

በላቸው፡፡

34|25|«ከአጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም፡፡ ከምትሠሩትም ሥራ አንጠየቅም» በላቸው፡፡

34|26|«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡

እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው፡፡

34|27|«እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእርሱ ያስጠጋችኋቸውን (ጣዖታት) አሳዩኝ፡፡ ተዉ

(አታጋሩ)፤ በእውነቱ እርሱ አሸናፊው ብልሃተኛው አላህ ነው» በላቸው፡፡

34|28|አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡

ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡

34|29|«እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡

34|30|«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን

አላችሁ» በላቸው፡፡

34|31|እነዚያ የካዱትም በዚህ ቁርኣን በዚያ ከበፊቱ ባለውም (መጽሐፍ) በጭራሽ

አናምንም አሉ፡፡ በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላለሱ ሆነው በጌታቸው

ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ፤ (አስደናቂን ነገር ታይ ነበር)፡፡ እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ

ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ አማኞች በኾን ነበር» ይላሉ፡፡

34|32|እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ከትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ

ከለከልናችሁን? አይደለም (እናንተው) ከሓዲዎች ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡

34|33|እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም፤ በአላህ እንድንክድና ለእርሱ

ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው» ይላሉ፡፡

221

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!