26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2|66|(ቅጣቲቱንም) ለነዚያ በስተፊትዋ ለነበሩትና ለነዚያም ከበኋላዋ ላሉት (ሕዝቦች)

መቀጣጫ ለፈራህያንም መገሰጫ አደረግናት፡፡

2|67|ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለ ጊዜ (አስታወሱ)፡፡

«መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን?» አሉት፡፡ «ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ»

አላቸው፡፡

2|68|«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡

«እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤

የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡

2|69|«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ

መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ ላም ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡

2|70|«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ይግለጽልን፤ ከብቶች በኛ ላይ

ተመሳሰሉብን፡፡ እኛም አላህ የሻ እንደኾነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን» አሉ፡፡

2|71|«እርሱ እርሷ ያልተገራች ምድርን (በማረስ) የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ

(ከነውር) የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ «አሁን በትክክል

መጣህ» አሉ፤ ሊሠሩ ያልተቃረቡም ሲኾኑ አረዷት ፡፡

2|72|ነፍስነም በገደላችሁና በርሷም (ገዳይ) በተከራከራችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ አላህም

ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው፡፡

2|73|«(በድኑን) በከፊሏም ምቱት» አልን፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም

ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡

2|74|ከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና

ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ ከድንጋዮችም ከርሱ ጂረቶች የሚፈሱለት አልለ፡፡ ከነርሱም በእርግጥ

የሚሰነጠቅና ከርሱ ውሃ (ምንጭ) የሚወጣው አልለ፡፡ ከነርሱም አላህን ከመፍራት የተነሳ ወደ

ታች የሚወርድ አልለ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ነገር ዘንጊ አይደለም፡፡

2|75|(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ

እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?

2|76|እነዚያንም ያመኑትን ባገኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ከፊላቸውም ወደ ከፊሉ ባገለለ

«ጊዜ አላህ በናንተ ላይ በገለጸላቸሁ ነገር እጌታችሁ ዘንድ በርሱ እንዲከራከሩዋችሁ

ትነግሩዋቸዋላችሁን? አታውቁምን?» ይላሉ፡፡

2|77|አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን የሚያውቅ መኾኑን አያውቁምን?

2|78|ከነሱም መጽሐፉን የማያውቁ መሃይማናን አሉ፡፡ ግን ከንቱ ምኞቶችን (ይመኛሉ)፤

እነርሱም የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡

2|79|ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት

«ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡

ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡

2|80|«እሳትም የተቆጠሩን ቀኖች እንጂ አትነካንም» አሉ፡፡ «አላህ ዘንድ ቃል ኪዳን

ይዛችኋልን? (ይህ ከኾነ) አላህም ኪዳኑን አያፈርስም፤ በእውነቱ በአላህ ላይ የማታውቁትን

ትናገራላችሁ» በላቸው፡፡

2|81|አይደለም (ትነካችኋለች)፤ መጥፎን (ክሕደትን) የሠራ በርሱም ኃጠኣቱ የከበበችው

ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡

2|82|እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ

በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡

11

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!